በጥርስ ህክምና ከመመርመር በፊትና በሁዋላ የሚሰጥ ትእዛዝ ፡

የጥርሳቸው ዲንጋይ ለማጽዳትና ፈገግታቸውን የማረ እንዲሆንላቸው ለማድረግ ጥርሳቸው ለማስተካከል ጥርስ ህክምና የሚሄዱ ሰዎች ብዛት በርካታ ነው፡፡ ይህ ሲያደርጉ ግን የማያውቁት ነገር አለ፡፡ ከሁሉም በማስቀደም የጥርስ ህክምናው አላማ ጠአፍና የጥርስ ጤና መጠበቅ መሂኑና ከዛም አልፎ በአጠቃላይ የታካሚው ጤና መጠበቅ መሆኑ ነው፡፡

ጥርስ ህክምና ከማድረግ በፊት መደረግ ስላለበት ነገር ፡

ጥርስ ሃኪም ለመሄድ ምን ኣይነት ዝግጂት ያስፈልጋል ?  ከጥርስ የሚቀረው የምግብ ርፍራፌ ለማጽዳትና የኣፍን ሺታ ለማሳደስ ወደ ህክምና ጣቢያው ከመድረስ በፊት ጥርስን በቡሩሽ መቦረሽ ያስፈልጋል፡፡

ማወቁ ኣስፈላጊ የሚሆነው ምንድን ነው ?

ጥርስ ሀኪም ከሚሄዱት ኣብዛኛ ታካሚዎች የህክምናው ኣላማ ፤የጥርስ ህክምና ኣላማ የቫክተሪይሙ ስራ መሰረት የሆነው የጥርስ ድንጊያ ማውጣት መሆኑ ኣያውቁም፡፡ የጥርስ ድንጊያ ማውጣት የጽዳቱ ቡሩሽ በጥርስና የጥርስ ስር የሚገኘው ባክትሪ ለማውጣት ቡሩሹ መግባቱ የካላከለዋል፡፡ የጥርስ ድንጋዩ እራሱ በጥርስ ስር ቁስል የሚፈጥር ፤ ሲቦርሹት እንዲደማ የሚያደረግ ሁኔታና የኣፍ ሺታ ይፈጥራል፡፡ የጥርስ ሀኪም ተጨማሪ ስራ የኣፍና የጥርስ ጤንነት ለመጠበቅ በጥርስ የተሰካው ባክትሪ ማንሳት::

ያማልን ?

እየአንድ አንዱ ታካሚ ሲታከም ምን ያህል ያመዋል የሚል ብቻ ሳይሆን የጥርሱና የጥርሱ ስር ጤንነት ምን ያህል ነው የሚለውም ነው፡፡ የጥርስ ስር ጤንነት እስከዛም አጥጋቢ ባልሆነ ቁጥር ህመሙ በዛ መጥን ነው፡፡ዕድሚያቸው ገና በሚወለድበት ክልል የሆኑ የጥርስ ህክምና የሚያደርጉ ሴቶች በሆርሞን ከፍተኛ እንቅስቃሴ ምክንያት መታመማቸው ከተለመደው የባሰ ይሆናል፡፡ የዚህ መፍትሄ ምንድን ነው ?ኣልሀሽ የሚባል ጥርስ ላይ ‌እንዲቀባላችሁ ሀኪሙን ጠይቁ፡፡

የህክምናው መጠናቀቅ ፡

.የታካሚ ጤና ታሪክ

ታካሚው ህክምና ከመጀመሩ በፊት ጤናውና የጤናው ታሪክ በተመለከተ ኣጭር የሚሞላ ፎርም መሙላት አለበት፡፡ እንደ የልብ ድካም ፤ ቁስል እና የተለያዩ የቀዶ ጥገና ህክምና የመሳሰሉ ኣድርጎ ከነበረ ጥርስ ህክምና ከማድረጉ በፊት አንቲቢዮቲክስ መውሰድ ይገደዳል፡፡እንደ የደም መርጋት ወይም ቆሻሻ ደም ማጥራት የመሳሰሉ ልዩ ትኩረት ያስፈልጋቸዋል፡፡

ጨርሶ የማይድንና ሁል ጊዜ መድሀኒት በመውሰድ የሚኖር በሺታና ወይም ጥርጣሬ ካለ ጥርስ ህክምና ከመደረስ በፊት ማጣራት እና የሚነገርህን መሰራት ያስፈልጋል፡፡ በነዚህ ምክንያቶች የመዘጋጀት ምርመራ ሊያስፈልግ ይችላል፡፡

የጥርስ ህክምና ባለ ሞያ (ዴንታል ሀይኒስት) ችሎታዋ ምንድን ነው ;    

ጥርስ ማጽዳት ፤ መቦረሽ ፤ የጥርስ ድንጋይና ሌላ በጥርስ የገቡ ነገሮች ማንሳት ፤ በጥርስ ስር ውስጥ እንደተያያዘ የቀረ ነገር በሃኪም ትእዛዝ እንዲለቅ ማድረግ፡፡

በገባው አርተፊሻል ጥርስ የቀረ ለማጣበቁ የሚጠቅም ትርፍ የጥርስ ህክምና ጭቃ ማንሳት ፤ በጥርስ ሞረድ ጥርስ ሞርዶ ማለስለስ ፤ በጥርስ ላይ የተሰፋ ክርና ጨርቅ ፈትቶ ከአፍ ማውጣት ፤ በአፍ የሚቀባ ማደንዣ መጠቀም፤ ማማከር ፤ የአፍና የጥርስ ጤና በተመለከተ ማስተማርና ማማከር –ስለሆነ የሚመቸው ለመምረጥና አጠቃላይ አጠቃቀም ለመማር ወደ ጥርስ ህክምና የጤና ጣቢያ ቡሩሽና ሌላም ለአፍና ለጥርስ ጽዳት የሚጠቅሙ ነገሮች ይዞ መምጣት (መቅረብ) ፡፡

ከየጥርስ ማስተካከል ባለ ሞያ (ዴንታል ሀየስት) ከመታየት በሁዋላ ምን ማድረ ያስፈልጋል ?

ከጥርስ ህክምና በሁዋላ ሊከተል የሚችል ነገር (ቶፋኦት ልቫይ) ፡

ብዙ የጥርስ ድንጋይ ይዞ የቆየ (የነበረበት) ጥርስ ድንጋዩ ተፍቆ ተነስቶ ሲገለጥ ወይም ከዛ በሁዋላ ብጥርስ ባለ ሞያ ከታየህ በሁዋላ ያለ መመቸት ሁኔታ ሊፈጥር ይችላል-እንደ ብርድ ብርድ የማለትም ጭምር ስሜት፡፡

የለቀቀው የጥርስ ድንጋይ የጥርሱ ስር በአፍ ውስጥ ክፍት ቦታ እንዲገለጥ አድርጓል-ወደ ጥርሱ ነርብ ስሜት የሚያሳልፈው፡፡

በዚህ አይነት ኣጋጣሚ የኤሌርጂጉ ስሜት በሚቀንስ የጥርስ ሳሙና መጠቀም፡፡ ወይም የዴንታል ሀየስቲቱ ክፍት በሆነው የጥርስ ስር ቅባት (ክሬም) ትቅቫ፡፡ ስሜቱ በጥርስ ስር ከሆነ እብጠቱና ስሜቱ ለማቃለል በጨው ውሀ አፍን ማጠብ ይቻላል፡፡

ፍሎሪድ

ፍሎሪድ ማለት በጥርስ ላይ የሚጣበቅ ተጨማሪ ነገር ሲሆን የተጎዳው ጥርስ የሚያዳጉስ ነው፡፡ ስለሆነ የጥርስ ህክምና በመደረግ ሂደት እያለህ ጥርስህን ከመጎዳት ለመከላከልና የሙቀትና የቅዝቃዜ አየር ለውጥ ይከላከል ዘንድ እንዲደረግልህ ትጠየቅ ይሆናል፡፡ እንዲሁም ፍሎሪዱ በጥርሱ ጎን ላይ ድንጋይ መፈጠሩ የሚከላከል ሲሆን ይህ ከመደረጉ በሁዋላ ለኣንድ ስኣት ያህል መብላትና መጠጠት ኣይቻልም፡፡

በጥርስ ላይ እንዴት የጥርስ ድንጋይ መፈጠሩ ማገት ይቻላል ;

በጥርስ ላይ የጥርስ ድንጋይ የመፈጠሩ ምክንያቶች ብዙ ሲሆኑ ከነሱ አንድ አንዶቹም ፤ የምራቅ ኣይነት ፤ ዘር  ፤ ምግብና የኣፍ ጽዳት ጥበቃ ናቸው፡፡ የጥርስ ድንጋይ መፈጠሩ ጭራሽ ማቆም አይቻልም፡፡ ግን የሚፈጠርበት ጊዜ እንዲራዘም ማድረግ ይቻላል፡፡ በጥርሶች መካከል እየገባ የሚቀረው ምግብ ለማውጣት በጥርስ ክር በመጠቀም እና ጥርስ በቡሩሽ በትክክል አጠቃቀም በመጠቀምና በየቀኑ ሁለት ጊዜ መቦረሽ በጣም የጥርስ ድንጋይ ላለ መፈጠሩ ይጠቅማል ፤ እንዲሁም ባክተሪ እንዳይፈጠር፡፡

በጥርስ ምልክት መፈጠሩ እንዴት መግታት ይቻላል ;

ቃፋኢንና የትንባኮ ዘር–ማለትም ኬተሙ የሚፈጥሩት ቡናና ሻይ ከመጠጣትና ሲጃራ ከማጨስ በተቻለ መጠን መቆጠብ በጥርስ ላይ ምልክት መፈጠሩ

ለተጨማሪ የመከታተል ምርመራ ወደ ጥርስ ህክምና ጣቢያው መቸ መመለስ ያስፈልጋል ;

ታካሚ ብጥርስ ባለ ሞያ የመታየቱ ጊዜ እንደ ጥርሱ ጤና ሁኔታ ሲሆን ታካሚ ሁሉ እንደየራሱ ሁኔታ ይሆናል፡፡ የጥርስ ችግር ከለለና አፍና ጥርስ ደህና ከሆኑ በየግማሽ ዓመት በጥርስ ህክምና ባለ ሞያ መታየት ይመረጣል፡፡ በጥርስ ስር ችግር በሚፈጠርበት ሁኔታ ግን በየስዎስት ወሩ ምርመራ ማድረግ ነው፡፡

ተጨማሪ ምን አለ ;

በጥርስ ባለ ሞያ መታየት ጥቅሙ የጥርስና የአፍ ጤና መጠበቅ ባቻ ሳሆን ለታካሚው ሰውነት ጤና በሙሉም ነው፡፡ ሰውነታችን ሁሉ ተከላካይ የጂማት ክሮች የለበሰ ነው–ለምሳሌ እንደ ቆዳችንና ጥፍሮቻችን ማለት ነው፡፡ ተከላካይ ጂማቱ ጥብቅ ያልሆነበት አንደኛውና ብቸኛው ቦታ የጥርሰና የጥርስ ስር መካከል ነው፡፡ ስለሆ በዚህ ጥብቅ ያልሆነና ክፍተት ያለበት ቦታ በኩል ባክተሪዎች

መግባት ከቻሉ በሁዋላ በደም በኩል አድርገው ወደ ሰውነታችን በማለፍ ብዙ በሺታ መፍጥር ይችላሉ፡፡  ለጨማሪ ጥያቄ ሁሉ ፤ ለአገልግሎትህ እንቆማለን– እኛ የሚያክምህ ሃኪም ፤ የህክምና ጣቢያው ሀላፊ እና ወይም የህክምና ጣቢያው የተገልጋዮች ክፍል ሀላፊ፡፡

የክላሊት ስማየል የህክማና ጣቢያዎች  ዝርዝር….

ጤናህን ቶሎ ይስጥህ !

ጤናችሁ ቶሎ እንድታገኙና ህክምናችሁ የተሟላ እንዲሆንላችሁ ክላሊት ስማየል ይመኝላች‰ል !