ከጥርስ ህክምና በፊትና በሁዋላ መደረግ ስለአለበት መመርያ፡

ይህን በተመለከተ ምን ማወቅ ነው አስፈላጊ የሚሆነው ; ህክምናው የሚያስከትለው ነገር ምንድን ነው; የህክምናው ከመደናቀፍ (ካለመቃናት) ምን ኣይነት ችግሮች ሊከተሉ ይችላሉ ? በመሰረታዊ የጥርስ ህክምና ሀኪሙ ወደ ጥርስ ስር እየገባ ቦታው ያጸዳል ፤ ያሰፋዋል እና ከዛ በሁዋላ የዘጋዋል፡፡ የዚሁ አይነት ህክምና በጥርስ ውስጥ (በውስጣዊ ጂማቱ) ወደ ምግል የሚል ችግር ሲፈጠር ወይም ጥርስ ሲደፈርስ ይረጋል፡፡ እንድ አንድ ጊዜም ጥርሱ ደህና እያለ ለእንክብካቤ ገጽታው ለመጠበቅ ሲባል ይደረጋል፡፡ ከንደዚህ ኣይነት ህክምና ህክምናው

በተደረገለት ጥርስ ላይ ተጨማሪ ጥርስ ይገባበታል፡፡

ከመሰረታዊ የጥርስ ህክምና በፊት የሚሰጥ ትእዛዝ ፡

ከዚህ ህክምና በፊት መብላት ይፈቀዳልን ; እንደተለመደው መብላት ይቻላል፡፡ ታካሚው ሺቅቭ የሚለው ከሆነ ግን ህክምናው ከመጀመሩ 3 ሳኣታት ቀደም ብሎ  –  ከባድ ምግብ መብላት አይመረጥም፡፡

 ሲታከሙ ያማልን? 

ህክምናው እራሱ የሚያም አይደለም፡፡ የደነዘዘው ቦታ ግን መደንዘዙ ካለፈ በኋላ ሲመለስ ሊያም ይችላል፡፡

 ስጋት ፤ ፍራቻ እንዴት መቋቋም ይቻላል? 

በርካታታካሚዎች ወደ ጥርስ ሀኪም መሄድ ይፈራሉ፡፡ መፍራቱ መቋቋም  በማይቻልበት ሁኔታ ህክምናው ከመደረጉ በፊት በሀኪም ፈቃድ ጸረ ፍራቻ መድሀኒት መጠቀም ይችላሉ፡፤ ህክምናው  ራስ በሚያስት መድሀኒት በመጠቀም ማድረግ የሚቻል ከሆነ ሀኪሙን አነጋግሩ፡፡

መሰረታዊ የጥርስ ህክምና በሚደረግበት ሂደት ላይ በታካሚው ጥርስ በተደጋጋሚ ራጂ ይደረጋል፡፡ የቆየ ያደረጋችሁት ራጂ ካላችሁ የዞ መምጣቱ ይጠቅማል፡፡

በተጎዳ ጥርስ የጥርስ ንጥረ ነገር ጨምሮ መስተካከያ ህክምና

ህክምና በሚደረግለት ጥርስ ቋሚ ማስተካከያ ጥርስ ካለ ህክምና ከመጀመሩ በፊት በጊዚያዊ ማስተካከያ ጥርስ መቀየሩ ይቻላል፡፡

መሰረታዊ የረጥርስ ህክምና ከማድረግ በሁዋላ የሃኪም ትእዛዝ ፡

ከመሰረታዊ የጥርስ ህክምና በሁዋላ ምን መብላትና መጠጣት ይፈቀዳል ;  

መሰረታዊ የጥርስ ህክምና ከማድረግ በሁዋላ ወድያውኑ ቀዝቃዛ መጠጥ መጠጣት ይፈቀዳል፡፡ሙቅ ምግብና መጠጥ (ውሀ) መጠጣት ግን ድንዛዜው ካበቃ በሁዋላ ነው

የሚቻለው፡፡ ድንዛዜው ከማብቃቱ በፊት ለጊዜው ከተራቡ ማኘክ የማስፈልጋቸው ቀዝቃዛ ምግቦች መብላት ይቻላል- እንደ ዩጉርትና አይስ ክሬም የመሳሰሉ፡፡

መሰረታዊ የጥርስ ህክምና ከማድረግ በሁዋላ ጥርስ በቡሩሽ ማጽዳት፡

መሰረታዊ የጥርስ ህክምና ከማድረግ በሁዋላ ወድያውኑ ጥርስ በቡሩሽ መቦረሽ ይቻላል-አዲሱ የገባው (የተተከለውው ) ጥርስ ጭምር፡፡

የጥርስ መሰረታዊ ህክምና ከማድረግ በሁዋላ የኣካል እንቅስቃሴ ፡

በህክምና አንጻር መሰረታዊ የጥርስ ህክምና ከማድረግ በሁዋላ የአካል እንቅስቃሴ (ጂምናስቲክ) ማድረግ ኣይከለከልም፡፡ የማመም ወይም የውጥረት ስሜት ካለ የስፖርት እንቅስቃሴ ሲደረግ ሊረብሽ ይችላል፡፡

መሰረታዊ የጥርስ ህክምናው በአንድ ጊዜ ካላበቃና በቀጣይነት ከሆነ በጥርሶች መካከል የሚገኘው እብጠት በሚፈጥረው ጋዝ ለውጥ ምክንያት እንቅስቃሴው ሊረብሽ  ይችላል፡፡

ህክምናው የሚያስከትላቸው ነገሮች ፡

ህክምናው በተደረገበት ቦታ የተደረገው መደንዘዝ ከመሰረታዊው ህክምና በሁዋላ መደንዘዙ ለሁለት ሳኣት ያህል ሊቆይ ይችላል፡፡ ከዛ በሁዋላም ለሳምንት ያህል የህመም ስሜት ሊኖር ይችላል፡፡ ማመሙ ምግብ ሲታኘክ ከትንሽ አለመመቸት እስከ ከባድ ህመም ሊደርስ ይችላል፡፡

ማመሙ እንዴት መቀነስ ይቻላል ;

መሰረታዊ ህክምና ከማድረግ በሁዋላ እስከ 48 ስኣታት የሚቆይ ህመም የተለመደ ነው፡፡ማመሙ ለማረጋጋት በሀኪም ፈቃድ ጸረ ማመም መድሀኒት መጠቀም ይቻላል፡፡

 መሰረታዊ የጥርስ ህክምና ከማድረግ በሁዋላ የሚፈጠሩ ያልተጠበቁ ችግሮች ፡

ጊዚያዊው የሚተከለው ጥርስ ከቦታው ተነቅሎ ከወደቀ ፤ ከተሰበረና ወይም እስከ ስኣታት የቆየ ህመም ካለ ህክምና መሄድ ነው፡፡

ህክምና ተሎ መሄድ የሚያስፈልገው ተጨማሪ ሁኔታ ህክምና የተደረገለት ቦታ ወደ መግል የሚል እብጠት ካሳየ ፤ ከሞቀና ከፍተኛ ሙቀትና እንደ መግል ያለ ነገር ካሳየ ሁኔታው የአንቲቢዮቲክስ መድሃኒት የሚያስፈለገው ከሆነ ነው፡፡

የምርመራ ጊዜ ፡

ጥርሱ የመቁሰል ነገር ካሳየ በየስድስት ወሩ ምርመራ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ምንም ነገር ችግር ከሌለ ዝም ብሎ ለምርመራ ብቻ በዓመት ኣንድ ጊዜ መመርመር ያስፈልጋል፡፡

መሰረታዊ የጥርስ ህክምና ከማድረግ በሁዋላ የአፍና የጥርስ ጤና፡

መሰረታዊ የጥርስ ህክምና ከማድረግ በሁዋላ የአፍ በየቀኑ ንጽህና ያስፈልጋል፡፡ ጥርስ ደህና አድርጎ መቦረሽና በቡሩሹና በጥርስ ውሥጥ የተሰካ ምግብ ማውጫ መጠቀም፡፡ በጥርስ የሚፈጠረው የጥርስ ድንጋይ ለማንሳት እንደ አገጭና ጥርስ ጤንነት ሁኔታ በዓመት ከሁለት እስከ ኣራት ጊዜ ጥርስ ህክምና ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

ምን ተጨማሪ ነገር አለ ?

የሚገባና የሚወጣ ጥርስ ከመደረጉ በፊት የተጎዳው ጥርስ ደካማ ስለሆነ ‌እንዳይሰበር ምግብ ከማኘክ መቆጠብ፡፡